Obituary

የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው መዝሙር 116:15

ወንድማችን አማን ስብሃት የፓል ቶክ መጠሪያ ስሙ “YeNigat Kokeb”በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ማክሰኞ ሜይ 22 2007 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡እግዚእብሔር የወንድማችንን ቤተሰብ እንዲያጽናና እንጸልያለን

Psalim 116:15 Precious in the sight of the LORD is the death of his saints.
Our Dear brother Aman Sibhat “YeNigat Kokeb” who was a very dear brother to all of Us has passed away due to car accident on May 22 2007 in winnpeg Canada. we pray for the comfort of his parents and family.

ሰላም ለናንተ ይሁን ቅዱሳን? እንደምን አላችሁ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን። በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ታላቅ ነውና። በእውነት ሁላችንም ብንሆን ስለ ንጋት ኮከብ ሞት አዝነን ነበር። ግን እግዚአብሔር በስራው አይሳሳትም። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ ትላንትናው ማለትም ሰኞ ቀን የቀብር ስነ ስርዓት በሆነበት ጊዜ ድረስ ቅዱሳን በያላችሁበት አዝናችሁ ስለነበር ይህንንም ነገር በቀጥታ ማስታላለፍ ስለወደድኩ በዚህ ሰዓት ደሞ አስተላልፋለሁ። ጌ እየሱስ ጌታ ነው! ወገኖቼ እኛ ማየት ያለብን ለምን ሆነ እንዴት ሆነ አይደለም። ለምን? የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው ፃድቅ ያልፋል የሚያስተውል ግን  ይላል። ስለዚህ እንድንናስተውል የእግዚአብሔር ሃሳብና ፍቃድ ነው። በዚህ ዘመን ወንድማችን ከመካከላችን በመጀመሪያ ቀን ሲለይ ሁላችንም አዝነን ነበር ግን በሁለተኛው ቀን ላይ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር በመካከላችን ሲያደርግ ስላየን ደስ ብሎናል። ይኽውም እንዴት ነው? በእኛና በኤርትራውያን መካከል ንግስት ባደረገው ሁኔታ ግኑኝነት አልነበረም እና ትልቅ የጥል ግድግዳ ነበር። ነገር ግን በንጋት ኮከብ ሞት ምክንያት እግዚአብሔርበቀን ሁለት ጊዜ ወንጌል በትግርኛና በአማርኛ ይሰበክ ነበር።

መገኛኘትም የማንችለውንም በአንድ አዳራሽ ውስጥ አስቀምጦ ይሄን የእግዚአብሔር መንግስት ሰራ እንዲስፋፋ አደረገ። በከተማችንም በድንቅ በታምራት ወንጌል ተሰበከ እኛም በጣም ደስ አለን። ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ነገሮችን በመልካም ቀየረው። ለምን ጻድቁን ወደ ራሱ ሰብስቦ ግን ለምንግስቱ ሰራ ምክንያቱም የሃጢያተኛውን ሞት የማይወደው እግዚአብሔር ለሃጢያተኞች የንስሃ ጊዜ ሊሰጥ ስለወደደ ይህን አደረገ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን በዚህ ደሞ ልንጽናና ይገባናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ምን አለ እኔ ብሔድ ይሻለኛል ለምን በዛ የተሻለ ቦታ አለ አለ። ወደ ተሻለው ቦታ ደግሞ ሁላችንም ለመሄድ እንሻለን እንናፍቃለንና ሰው ወደተሻለ ቦታ ሲሄድ ደስ ይለዋል እኛም በዚህ ነገር ደስ ብሎናል። ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ከኛ ቢለይ ግን የእግዚአብሔር ስራ ሲሰራ አይተን ደስ ብሎናል።

እኛም ወደዚሁ ወደ ጌታ እንሰበሰባለን ምክንያቱም ወንድማችን ንጋት ኮከብ የድንኳኑን ዘመኑንና ጊዜውን ጨርሶ ወደ አምላኩ ተሰብስቧል እኛም በግዚአብሔር ጊዜ ለዘላለም እናየዋለን። በዚህ ምክንያት ለሰባት ቀን ነበር ሃዘኑ በቤተ ክርስቲያን የተደረገው ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ አዳራሽ ስላዘጋጀ ከዛ የተነሳ ለሰባት ቀን ቢያንስ ሁለቴና ሶስቴ ከዚያም በላይ ወንጌል እየተሰበከ በተለያየ ቋንቋ ሲፀለይና ሲሰበክ ሙሉ ቀን እስከ እኩለ ሌሊት አብረን ከወገኖች ጋር በከተማው አብረን አሳልፈናል ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። ወገኞቼ በጣም ደስ ይል ነበር በሃዘንም ለካ እንዲ ያለ ሁሌታ አለ? እግዚአብሔር ለእኛ የጥሞና ጊዜ ነው ያደረገልን። መሰራት የማይገባው ነገር ሁሉ ተሰርቷል:: እግዚአብሔር ትልቅ ነው። በዚህም ደስ ይለናል ምን ጊዜም በምድር ላይ መኖራችን ለወንጌል ነው። የንጋት ኮከብ በጣም ዝምተኛ እና ምንም የማይናገር በመካከላችን ቢሆንም ነገር ግን በአገልግሎቱ እንባረክ ነበር።

ሌላው ትላንትና (ሰኞ) የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል ከቀብሩ መጀመሪያ በቤተ ክርስቲያናችን አስክሬኑ መጥቶ ስነስራቱ ሲፈጸም ብዙ ዝብ በተሰበሰበት አፕስቲር እና ዳውንእስቴር ያለው አዳራሽ ሞልቶ ነበር። ወንጌል በተጨማሪም እኔም እናንተን በመወከል ‘ኢትዮጲያን ፕላስ ኦል’ የፍቅር መግለጫ አበርክቻለሁ። የኤ እና የ ቢ መዘምራን ቆመው ዘመሩ ለተወሰነ ጊዜ እንደሚላያይ ሰው ሸኝተው እንደሚመለስ በዚህ መልኩ ሽኝተነው ተመልሰን በጣም ደስ በሚል ሁሌታ ስነስርዓቱ ተካሂዷል:: አብረንም የፍቅር ማዕድ ቆረስንና በመጨረሻም እስከ እኩለ ሌሊት ቆይተን ተለያየን። በጣም የሚገርመው ሰው ከሃዘን ሲለያይ እያለቀሰ ነው እንጂ እንደሰርግ ቤት ፎቶ እየተነሳ አይለያይም እኛ ግን ከቤተሰቡ ጋር ማስታወሻ ይሆነን ዘንድ ይህንን አድርገን ተለያየን። ማንም ወንድሙ ወይም ቤተሰቡ ሞቶበት እንደዛ አያደርግም እግዚአብሔር ግን ይህንን አደረገ ስለዚህ እናንተም ልታዝኑና ልታለቅሱ አይገባም። ለምን እግዚአብሔር ፍጹም እና ፃድቅ ስለሆነ ለክብሩ ለመንግስቱ ስፋት አድርጓልም ወንጌልም በኃይል ተሰብኳል። ስለዚህ ተስፋ እንደሌላቸው አይደለም አንድ ቀን እንገኛልን። በእህቱ እና በቤተሰቦቹ ስም ምስጋና አቀርባለሁ።

የእህቱም ስም ‘ሃሌ ሉያ’ በሚል ኒክ መጠሪያ ስም የምትገባ ናት። እግዚአብሔር ይባርካችሁ ስለ ፍቅር ስጦታችሁ ብላለች።

የማስተላልፈው የአብ ሥራ ነኝ ከካናዳ

 

ወንድም ተወልደ ዮሐንስ

ወንድም ተወልደ ዮሐንስ ከአባታቸው ከአቶ ዮሐንስ ተመልሶና ከእናታቸው ከወይዘሮ .ድስታ መድህኔ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የካቲት 24 ቀን 1938 ዓ.ም ሰገነይቲ በተባለው ከተማ ተወለዱ፡፡ዕድሜያቸው ለትምሕርት አንደደረሰ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኤርትራና በትግራይ ከተከታተሉ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በትግራይ አጠናቀው በ1956 ዓም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ1961 ዓ.ም ከፊዚክስ ዲፓርትመንት በባችለር ኦቭ ሳይንስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡በወቅቱ በነበረው ስርዓት መመሪያ ዬኒቨርሲቴ ተማሪዎች ተምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት የአንድ ኣመት የአገልግሎት ጊዜ መስጠት ስለነበረባቸው በ1960 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተመድበው አገልግለዋል፡፡

ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደስራ ዓለም በመሰማራት ከነሐሴ 1961 እስከ መስከረም 1971 ድረስ በአስበ ተፈሪ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነት

ከመስከረም 1963 እስከ እስከ ህዳር 1969 ድረስ በድሬዳዋ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነትና በምክትል ዲሬክተርነት

ከህዳር 1969 እስከ እስከ መስከረም 1 1978 በአዲስ አበባ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነትና በምክትል ዲሬክተርነት

ከኦገስት 1998 እስከ ጁላይ 2007 በበኹም ጀርመን በድህረ ምረቃ ትምህርትና በምርምር .ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በጀርመን አገር ቆይታቸውም በፊዚክስ የ.ማስተርስ ዲግሪያቸውን የሰሩ ሲሆን ዶክተሬት ዲግሪቸወወን ሰርተው በማተናቀቅ ላይ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም በኮምፒዩተር ሳይንስና በበርካታ የድኅረ ምረቃ ኮርሶች የምስክር ወረቀቶችን ተቀብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ነጻነት ባልነበረበት የደርግ ስርዓት እንዴት በክርስትና ህይወት እንዳሰለፉ ባለቤታቸው እህት ገነት እሸቴ እንዲህ በማለት ይገልጹታል…. ተወልደ ዮሐንስ በአዲስ አበባ የሕይወት ብርሃን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሆኖ ሰርቷል፡፡ በዚያን ጊዜ በደርግ ስርዓት መሠረተ ትምህርት በየቀኑ ማታና እሁድ ጠዋት ማስተማር ግዴታ ነበር፡፡ ወንድም ተወልደ ግን

የእሁድ ጠዋቱ የማስተማር ፕሮግራም ከቤተ ክርስቲያን ስለሚያስቀረው አያስተምርም ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ከደርግ ጋር ብዙ ችግር ፈጥሮበት ነበር፤ በከፍተኛ፣ በቀበሌና በመጨረሻ ላይ 3ኛ በተባለው ሰውን እየወሰዱ በሚጨርሱበት ቦታ ሁሉ ታስሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ መርማሪው ፖሊስ ለምን እሁድ ጠዋት መሠረተ ትምህርት እንደማያስተምር ሲጠይቀው በቤተክርስቲያን

የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምራቸው ሰዎች ስላሉ እንደሆነ መለሰለት፡፡ በዚያን ጊዜ ፖሊሱ አንተ እዚያ የምታስተምረውን ነገር እኔም ድሮ እማር ነበር፤ አንተ ሃቀኛ ሰው ነህ ብሎ ከ3 ቀን በኋላ ከእስር ፈታው፡፡

በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ፖሊሶችና ካድሬዎች የትምህርት ቤቱን ቻፕል ለደርግ የስብሰባ አዳራሽ መጠቀሚያ ለማድረግ ካልሰጠኸን ብለው ሲመጡ፤ እንዲሁም ክርስቲያኖችን በእምነታቸው ምክንያት ለመያዝ ሲመጡ በእኔ ደም ተራምዳችሁ ነው ይህን የምታደርጉት ብሎ ሁልጊዜ በድፍረት ጠመንጃ ከያዙ ሰዎች ጋር ከፊት የሚጋፈጥ ሰው ነበር፡፡ በጌታ እጅግ ስለሚተማመንና በዚህ ድፍረቱ

አዳራሹን ደርግ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

በድሬዳዋ ልዑል መኮንን ትምህርት ቤት ምክትል ዳይሬክተርና መምህር ሳለ፣ ተማሪዎችን ትምሕርት ሲያቆሙ መማርና መሥራት እንዳለባቸው ሲያደፋፍር ተማሪዎች ከፎቅ ላይ እባብ ወርውረውበት ነገር ግን ምንም ሳይሆን ተርፏል፡፡

2ኛዋ ልጃችን በሁለት አመቷ አባቷን በጠመንጃ አስፈራርተው በጂፕ መኪና ሲወስዱት ስላየች እስካሁን ድረስ የወታደር ልብስ እንኳ ስታይ ትረበሻለች በማለት ገልጸውልኛል፡፡

ወንድም ተወልደ ዮሐንስ በቅርብ ለሚያውቃቸውና ለተጠጋቸው ብቻ ሳይሆን በአጪር ጊዜ ቅርበት ብቻ ለተጠጋቸው ሰው በእርግጥም ራሳቸው የሚነበቡ ወንጌል መሆናቸውን ለመረዳት ብዙም አይወስድበትም፡፡

ወንድም ተወልደ በመላው አውሮፓ በተቋቋሙት የክርስቶስ ቤተክርስቲያናት ውስጥ በችግርም ሆነ በደስታ ጊዜ ቀድመው በመገኘት በአርአያነት የሚጠቀሱ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው የአምነት አባትና ሃዋርያ ነበሩ፡፡ ወንድም ተወልደ ዮሐንስ ከባለቤታቸው ከእህት ገነት እሸቴ ሕድዓት : ምስጋና,አወት,ምህረትና,ዘካርያስ የሚባሉ 5 ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ምንም እንኳን ወንድም ተወልደ ዮሃንስ በአባታቸው ዕቅፍ ውስጥ ለዘለዓለም ለመኖር በድል የተሰናበቱን ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው መሆናቸውን በማሰብ ብንጽናናም በአውሮፓ የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያንና መላው ዓለም የሚገኙ ወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በክርስቶስ የሆኑ ወገኖቻቸው ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፤ታላቅ ወንደም መካሪና አጽናኝና አጥተዋል፡

፤እግዚአብሔር መጽናናትን ለቅዱሳን ሁሉ እንዲሰት ጸሎታችን ነው፡

 

የፓስተር አቤል ገብሬ አጭር የሕይወት ታሪክ

ሴፕቴምበር 27 2008 በሔልሲንኪ ፊንላንድ በተደረገው የመሰናበቻ ፕሮግራም ላይ ከተነበበው የሕይወት ታሪኩ የተወሰደ

ጌታ ኢየሱስ አልዓዛርን ከማስነሳቱ በፊት ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ እንኳን ቢሞት ህያው ይሆናል ህያው የሆነም የሚያምንብኝም ለዘላለም አይሞትም ነው ብሎ የነገረን፡፡ወንድማችን ፓስተር አቤልም በትምርቶቹም ሆነ በዝማሬዎቹ ዘላለማዊነትን ህያውነትን አስረግጦ ነበር የሚናገረው;;ዛሬ በተራው ወደ ሚወደው ጌታ ቢሄድም ዛሬም መልክቱ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ነው

ፓስተር አቤል ገብሬ 1960 ዓ.ም በወሎ ጠቅላይ ግዛት ተወልዶ ዕድገቱንና መኖሪያውን ያደረገው ግን በአዲስ አበባ ነው፡፡ዕድገቱ በአጎቱ ቤት ቢሆንም ከምስክርነቱ እንደተረዳነው ብዙ ጊዜ የኖረውና ልጅነቱን ያሳለፈው እራሱን እየረዳ በራሱ እንደነበር ብዙ ጊዜ ይናገር ነበር፡፡

ታዲያ አንድ ቀን በሚገርም ሁኔታ በእስር ቤት እንዲገባ ሆነ በእስር ቤትም ግማሹ በወንጀል የገባ ሲሆን ጥቂቶች ደግሞ ጌታን በማመናቸው በዛ በእስር ቤት የነበሩ ወገኖች ጌታን በእስር ቤት እያሉ ሲመሰክሩለት እንኳን የያንዳንዱ ክርስቲያን ፈገግታ የያንዳንዱ ክርስቲያን ህይወት ይማርከው እንደነበር ብዙ ጊዜ ይመሰክር ነበር;;

ከዛም በእስር ቤት እግዚአብሔር በልዩ መንገድ እንዳገኘውና ፓስተር ግርማ ቦጋለ በዚያን ጊዜ ወንጌላዊ በእምነቱ እንዲጠነክር እግዚአብሔር እንደተጠቀመበት መስክሮአል;;ላገኘውም ጌታ እንዲህ ብሎ ዘምሯል፡፡



ያለፉትን ቀኖቼን ሁሉ ዞሬ ስመለከት

አሳየኝ ፍቅር ጌታን ሚዛን አጣሁለት

ታማኝ ሆኖ አቅፎ ላቆመኝ ክንድህ

ቁርባኔን ተቀበል ክበርልኝ ስልህ

ሰውነቴ ጠፍቼ አልቀረሁም ብላ እንድትመሰክር

በጸጋህ ሰጥተሃታልና የዘለዓለም ክብር

በእስር ቤት ቆይታው እግዚአብሔር ለሱ በሚገባው መንገድ ተናግሮት ከመጽሐፍ ቅዱስ በቀር ሌላ እንዳያነብ ቃል በመግባቱ በጥቂት ጊዚያት እግዚአብሔር አሳድጎት መዝሙርም ሰጥቶት ጊታርም መጫወት ችሎ ከእስር ቤት ወጣ;; ከእስር ቤትም አንደወጣ በብዙ ወገኖች ፍቅርና እንክብካቤ ውስጥ ሆኖ አገልግሎቱን ቤት ለቤት ጀመረ;; በዚያን ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን የነበረው ስርአት አስዘግቷቸው ስለነበረ ወገኖች የሚያመልኩት በየቤቱ ነበር;; ፓስተር አቤል በመሰጠት በከተሞችም በገጠርም እየተዘዋወረ ከወገኖች ጋር ወደ ፊንላንድ እስከመጣበት ዕለት ድረስ አገልግሏል፡፡

ፓስተር አቤል በተፈጥሮው አስተዋይና በእጆቹ ብዙ ነገሮችን መሳል መቅረጽ ማነጽ ይችል ስለነበረ በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ በእጁ ሰርቶ ሐዋርያው ጳውሎስ ድንኳን እየሰፋ ያገለግል እንደነበር የሚያገኘውን ገንዘብ ሁሉ በእምነታቸው ምክንያት በስደት ያሉትን ወንድሞች ሰብስቦ አብሮ በመኖር በመርዳትና በተረፈው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እየገዛ ያድል እንደነበር የሚያውቁት ትዝታ ነው፡፡
 
በኢትዮጵያ ውስጥ በልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለጥቂት ጊዜያት የሰራ ሲሆን ወደ ፊንላንድ ከመምጣቱ በፊት በኖርዌጂያን ቤተ ክርስቲያን ዕርዳታ ድርጅት ውስጥ ይሰራ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ በ1989 ዓ.ም ወደ ፊንላንድ በር ከፍቶለት ጌታ እንዴትና በምን መንገድ እንደሚያገለግል በግልጽ ነግሮት እንደመጣ መስክሮልናል፡፡ ይህም ድግሞ ለአገልግሎቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ነበረው፡፡ ወደ ፊንላንድ እንደመጣ እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ጀምሮት ለነበረው አገልግሎት በወንጌላዊነት ወደ ትልቅ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ እግዚአብሔር ተጠቅሞበታል;;

እግዚአብሔር የሰጠውንም ትምህርትና ዝማሬ ጥቂት ለነበሩ ወገኖች በማካፈል የዝማሬ አገልግሎት በወገኖች ቤት ውስጥ እንዲጀመር አድርጎ በፊንላንድ ያለች ቤተክርስቲያን እንድትጠነክር ሌት ተቀን ሰርቷል;;ትንሽ የነበረው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወደ ጠንካራ ህብረት እንዲለወጥ ጌታ ተጠቅሞበታል;;

ይህንንም ያዩ የፊንላንድ ወገኖች በ1991 በወንጌላዊነት እንዲያገለግላቸው ወስነው ይህንንም ስርዓት ፓስተር ሃይሌ ተገኝተው እንዲያስፈጽሙ በተጠየቁት መሠረት ስርዓቱን አከናውነው ይህም አገልግሎቱ እንዲሆን ተደርጎ እስከ 2005 ዓ..ም በወንጌላዊነት አገልግሏል;; ከዚያም በ2005 የፊንላንድ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን አባላት ፓስተር ሆኖ እንዲያገለግል በሙሉ ድምጽ በማጽደቃቸው ፓስተር ዳንኤል መኮንን ተገኝተው የመጋቢነቱን የሹመት ስርዓት አከናውነዋል፡፡ ፓስተር አቤል ገብሬ ወደ ጌታ እስከሄደበት ድረስ ፓስተር ሆኖ አገልግሏል፡፡

ፓስተር አቤል በቤተሰብ ህይወቱ በ1991 እህት አንን አግብቶ 3 ወንድ ልጆችን ወልዷል፡፡ እግዚአብሔር በሰጠው ዘመን ውስጥ እስካንቀላፋበት ጊዜ ድረስ ቤተሰቡንና ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግሎ በተወለደ በ48 አመቱ አንቀላፍቷል፡፡https://www.youtube.com/watch?v=0l2NCFTv6hg

 

አልማዝ ዘለቀ

በጌታ የተወደደች አህታችን አልማዝ ዘለቀ ባደረባት ሕመም ምክንያት በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ዲሴምበር 25 ቀን 2008 ዓ.ም በተወለደች በ 28 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡አህታችን አልማዝ በ Paltalk Ethiopian Christians Plus All
ክፍል በጸሎት አገልግሎት ተሰማርታ ወደጌታ እስከተሰበሰበችበት ቀን ድረስ በቅንነት ስታገለየቆየች አህት ስትሆን በዚህ አገልግሎት የተሰማራን ሁሉ እሷን በማጣታችን ተጎድተናል አዝነናል፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር በስራው የማይሳሳት ጻድቅ አምላክ በመሆኑ እህታችንወደተሻለ፣ ሃዘንና ለቅሶ ወደሌለበት ወደተሻለ ዓለም እንደሄደች በማመን እንጽናናለን፡፡

በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኢንተርኔት ሚንስትሪ፣ የEthiopian Christians Plus All ክፍል አገልጋዮችና ተሳታፊዎች ለእህታችን አልማዝ ዘለቀ ቤተሰቦች እንዲሁም በአምስተርዳምና በአጠቃላይ በሆላንድ ለሚገኙ ቅዱሳን ሁሉ እግዚአበሔር ያጽናችሁ በማላት የተሰማንን ልባዊ ሃዘን እንገልጻለን፡፡

 

እህት ሐና ታደሰ

የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው መዝሙር 116፡15


የእህት ሐና ታደሰ አጪር ህይወት ታሪክ

እህት ሐና ታደሰ ከአባቷ ከአቶ ታደሰ ተገኝና ከእናቷ ከወይዘሮ ዘውዲቱ መንግስቱ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ታህሳስ 23 ቀን 1967 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደች፡፡ዕድሜዋ ለትምሕርት እንደደረሰ አንደኛ ደረጃ ትምሕርቷን በብርሃነ ዛሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማረች በኋላ በ1988 ዓም ወደ ሆላንድ አገር መጥታ መኖር ጀመረች፡፡በዚህ በሆላንድ ቆይታዋ በረዳት ነርስነት ትምሕርት በመከታተል በዲፕሎም ተመርቃለች፡፡

ከዚያም ዛል ቦሙል በሚባል ከተማ በሚገኝ ቪለቫል የአዛውንቶች መንከባቢያ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ወደ እንግሊዝ አገር እስከሄደችበት እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ በታማኝነት ስትሰራ ቆይታለች፡፡ እህት ሐና በዚህ መስሪያ ቤት በሰራችባቸው 7ዓመታት ውስጥ በስራ ባልደረቦቿ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት የነበራት እህት ነበረች፡፡የስራ ባልደረቦቿ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ሲሰሙ በየእለቱ እየደወሉ በማልቀስና በማዘን ልባዊ ሃዘናቸውን የገለጹ ሲሆን ይህም እህት ሃና በወገኖቿ ኢትዮጵውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ዜጎች ዘንድ ተወዳጅነት የነበራት እህት እንደነበረች ያረጋግጣል፡፡

በእንግሊዝ አገር መኖር ከጀመረችበት ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ኮፐር ሂል ሬዚዴንሻል ኤንድ ነርሲንግ ሆም በተባለው ድርጅት ተቀጥራ ሕይወቷ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ስታገልግል ቆይታለች፡፡

አህት ሐና ጌታን ገና በ12 ዓመት ዕድሜዋ የተቀበለች ሲሆን በእምነቷ ጽኑና ተግባራዊ የክርስትና ሕይወት የነበራት ከሩቅ የሚታይና የሚያንጸባርቅ የክርስትና ሕይወት ያላት እህት ነበረች፡፡

እህት ሐና ሰውን የመርዳት በተለይም በጌታ የሆኑትን ሁሉ ባላት ነገር ሁሉ የመደገፍና የመርዳት ልዩ ጸጋና የተከፈተ ልብ የነበራት እህት ነበረች፡፡ለዚህም ከዚህ ዓለም በሞት የመለየቷ ዜና እንደተሰማ ከደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ከግብጽ ከህንድና ከተለያዩ አገሮች ካሉ በርካታ ወገኖች እህታችን ያደረገችውን መልካም የፍቅር አገልግሎት በማስታወስ በእንባ እየታጠቡ ሃዘናቸውን በስልክና

በኢንተርኔት መስመር በተከፈተው የፓልቶክ ድረ ገጽ የሰጡት ምስክርነት በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

እህት ሐና ጌታን እያገለገለች ቅዱሳንን እየደገፈችና እየረዳች በፈገግታዋ እያጽናናችና እያበረታታች በመፍትሔ ፈላጊነትዋ የቀረቧትን ሰዎች ሁሉ ልብ እየሳረፈች በመመላለስ ላይ እያለች በደረሰባት ድንገተኛ አደጋ ማርች 16 ቀን 2008 ዓም በእንግሊዝ አገር በሊድስ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

እህት ሐና ታደሰ በለጋ ዕድሜዋ ከመካከላችን መለየቷ እጅግ አስደንጋጭና ልንሸከመው ያልቻልነው መሪር ሃዘን ቢሆንብንም ከልጅነት ጀምሮ በታመነችውና በተከተለችው ጌታዋ ዕቅፍ ውስጥ መሆኗን በመረዳት እንጽናናለን፡፡

በከርስቶስ ኢየሱስ ሆነው የሚያንቀላፉ ተስፋ ያላቸው ለነሱ ሞት ወደ ህይወት የመሸጋገሪያ በር እንጂ አንቆ ሊያስቀር የማይችል የተሸነፈ በመሆኑና ሞትን ያሸነፈው ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ሕያውና የሆነና እህታችንንም በእቅፉ የተቀበለ በመሆኑ በዚህ እንጽናናለን፡፡ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም በቃሉ ሲናገር ”እኔ ትንሳኤና ሕይወትነኝ በኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል” ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 11፡25 ብሏል

እህት ሐና ገሊላ ጌቱ የተባለች የ10 ዓመት ልጅዋን ትታ የሚወዷትን ቤተሰቦቿን ተነጥላ መሄዷ በስጋ ቢያሳዝንም የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና ዕውነት እንዲሁም ዘለዓለማዊ ስለሆነ እህታችን ሐና ዛሬ በስጋ ብትለየንም በመንፈስ ደግሞ ሕያው ስለሆነችና በጌታ ቀን ስለምንገናኝ በዚህ እንጽናናለን፡፡

በዚህ ቀን ለእህት ሐና ቤተሰቦች እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ ጸሎታችን ነው