Words from the founder of Ethiopian Christians Internet Ministry

Pastor. Yohannes Teffera

Pastor Yohannes Teffera with all ECIM members greet you warmly in the name of our Lord Jesus Christ. It is a privilege for us to extend a warm welcome to our website. I hope it would be useful and above all, by the grace of God, it would be a great blessing. Our main desire is to present the message of salvation that our Lord Jesus Christ commanded to his disciples in Matthew 28: 19-20.

ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ

ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ (ኦሪትዘጸአት 8፡1) የሚለው ቃል በባርነት ተይዞ የነበረውን የእስራኤል ሕዝብ ከፈርዖን ለማስለቀቅ የተሰጠ አምላካዊ ትዕዛዝ ነው፡፡
ዛሬም በመንፈሳዊ ዕስራት ውስጥ ተተብትቦ ያለው ሕዝብ የባርነት ሃሳብና እስራት ውስጥ ሆኖ ለአዲሱ መንፈሳዊስርዓት ግንባታ ምንም አስተዋጽዖ ሊያበረክት አይችልም፡፡የግብጽ አስተሳሰብ የባርነት አስተሳሰብ ነው፡፡በግብጽ በባርነትውስጥ የነበሩ እስራኤላውያን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ቀኑን የት እንደሚውሉ ምን እንደሚሰሩ ዕቅድ የማውጣት መብትአልነበራቸውም፡፡
እስራኤላውን በስደት ዘመናቸው ጌቶቻቸው ግብጻውያን በወሰኑት ውሳኔ ውስጥ፣ ያለ ምንም ምርጫ፣ ባልፈለጉትናባላመኑበት ቦታ፣ ሕይወታቸውንና ጉልበታቸውን የሚያውሉ ነበሩ፡፡
ክርስቲያኞች ይህን ከመሰለ የዓለም ባርነት “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነትእንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9ተብሎ እንደተጻፈ የተጠራንበት ዓላማና ግብ ደግሞ፣ የእርሱን በጎነት ለመናገር፣ለንጉሥ ካህናትና፥ ለቅዱስ ሕዝብነት ፥እንዲሁም ለርስቱ የተለየ ወገን ልንሆን መሆኑን አውቀን ነጻ ለመሆን እንደተለቀቀ ሕዝብ ኖረን ለማረፍ ሕይወታችንንእናስተካክል ዘንድ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ልንወስን ይገባል፡፡

በቃሉን የተሰጡ አምስት ተስፋዎች

ያለማቋረጥ እግዚአብሄርን በቃሉ ውስጥ እና በጸሎት ይፈልጉታል ? ወይስ ብዙ ጊዜ ሞክረው ተስፋ በመቁረጥ ምክንያት እጅ ሰጥተዋል ? ይህ የብዙዋቻችን ታሪክ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ሊኖርህ ይችላል፡፡ ይሁንና ግን ጊዜ ሕይወት ሰጪ ነው? ወይንስ እንዲሁ ለመርሃ ግብሩ ሲባል ፣ ወይም የተሰጠንን የቤት ስራ ለመጨረስ ብቻ ፣ ወይም የጸሎት ደብተር ላይ የሰፈሩትን ርዕሶች ለመጨረስና ከዚያም እፎይ ተገላገልኩ የማለት አይነት ነው?

ይህን ሁኔታችንን ለመቀየር ጊዜው አልዘገየም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ለመውሰድ ፈልገው ትግል ላይ ከሆኑ ሊያግዞት የሚችሉ አምስት ተስፋዎች እነሆ፡፡ አግዚአብሄር ተዝቆ የማያልቅ ደስታ ነው “ብርሀንህን እና እውነትህን ላክ ፤ እነርሱ ይምሩኝ ፣ … ወደ እግዚአብሄር መሰዊያ ፤ ጎልማሳነቴን ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ ” እግዚአብሄር የተትረፈረፈ ደስታ እንደሚሆነን ሲናገር ሊሰጠን ያለውን ስጦታ በማየት ሳይሆን ማንነቱን በማሰብ ነው፡፡ እረሱን ስናስብና ስናመልከው ከምንም የሚልቅ የማያልቅ ደስታ ይኖረናል፡፡ ታዲያ ስለምንድን ነው እርሱን ከመፈለግ ይልቅ መኝታን የምንመርጠው ? ምክንያቱ እርሱ የላቀ የደስታ ምንጭ መሆኑን ስላላመንን ነው፡፡ ስለዚህስ ምን ማድረግ አለብን ? ጥርስን ነክሶ ከመሞከር ይልቅ ዘማሪው ያለውን ማድረግ ይበጃል፡፡ እግዚአብሄር ብርሃኑን (ልብን የሚያበራን የመንፈሱን ስራ) እና እውነቱን (የእግዚአብሄርን ቃል) እንዲልክ እንጠይቅ፡፡ በመዝሙር 43፡3-4፣ 16፡11 ፣ ማቴዮስ 13፡44 እና 1ጴጥሮስ 1፡8 የመሳሰሉት ክፍሎች ላይ እግዚአብሄር ደስታችን ስለመሆኑ የተሰጡትን የተስፋ ቃል በመያዝ እንጸልይ፡፡ ይሄን ስናደርግ በእውነት እግዚአብሄር ብርሀኑንና እውነቱን ይልካል፡፡ እርሱ ከምንም የላቀ ዘላለማዊ ደስታ መሆኑንም ስንረዳ የበለጠ ከርሱ ጋር ጊዜ መውሰድን እንናፍቃለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት እምነትን ይጨምራል ‘’እንግዲህ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው’’ (ሮሜ 10፡17) እምነቴ የደከመ መስሎ ስለሚሰማኝ ብዙ ማለዳዎችን እግዚአብሄርን ባለመፈለግ ተፈትኛለሁ፡፡ ያ ግን ህመም ስለተሰማኝ ዶክተር ጋር አልሄድም የማለት ያክል ነው፡፡ ልክ አንድ ዶክተር ህመምተኞችን እንደሚያክም ሁሉ እግዚአብሄርም በቃሉ አማካኝነት የደከመ እምነትን ያበረታል፡፡ ደካማ እምነት እንደ ደከመ ባትሪ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ደግሞ እንደ ባትሪ መሙያ ነው፡፡ እምነታችን ሲደክም በቃሉ የባትሪ መሙያ ላይ በመሰካት ለማደስ እንችላለን፡፡ ከቃሉ ጋር የማያቓርጥ ህብረት ሲኖረን እምነታችንን እንደሚያድስ ቃል ገብቶልናል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ብቸኛና ፍጹም የሆነ የምሪት ምንጭ ነው፡፡ “ህግህ ለእግሬ መብራት ፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው”(መዝ 119፡105) አለም ድቅድቅ ጨለማ በዋጠውና አንዳች የሚታይ በሌለበት ዋሻ ትመሰላለች፡፡ እግዚያብሄር ግን በዚህ ጨለማ ውስጥ አጥርተን ማየት የሚያስችለንን የቃሉን “ባትሪ” ሰጥቶናል፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሄርን ቃል ሳናጠናና ሳናሰላስል ቀናችንን መጀመር ማለት በድቅድቁ ዋሻ ውስጥ ባትሪያችንን ሳናበራ እንደመዳከር ነው፡፡ በተቃራኒው ቀናችንን የእግዚአብሄርን ቃል በማጥናት ስንጀምር ባትሪችንን በዚህ ጨለማ በዋጠው ዋሻ ውስጥ እንደማብራት ነው፡፡ ያኔ በፊታችን ያለውን ጉድጉአድ ወይም እንቅፋት አጥርተን ስለምናይ ወደ ተሸለው መንገድ አቅጣጫችንን መለወጥ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ባትሪዋን ሳያበሩ የቀን መንገዶን አይጀምሩ፡፡ ስንጸልይ እግዚአብሄር ይመልሳል ‘’ለምኑ ፣ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ ፣ ታገኙማላችሁ፤ መዚጊያን አንኩአኩ ይከፈትላችሁማል’’ (ማቴ 7፡7) የማንጸልይበት አንዱ ምክንያት እግዚአብሄር ጸሎትን አይሰማም የሚለውን የሰይጣንን ውሸት ስለምንሰማ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ያስተማረው ግን ያንን አይደለም (ማቴ 7፡7) ስንጸልይ እግዚአብሄር የጸሎታችንን መልስ እንደሚመልስልን ጌታ ኢየሱስ ቃል ገብቶልናል፡፡ የጸሎታችን ምላሹ ባንጠይቅ ኖሮ የማናገኘውና የጠየቅነውን ራሱኑ አሊያም ከዛ የተሸለ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በማለዳ ስለ ልባችን ፣ ስለ ትዳራችን ፣ ስለ ልጆቻችን ፣ ስለ ስራችን ፣ ወይም ስለ አገልግሎታችን ስንጸልይ እግዚአብሄር ባንጠልይ ኖሮ የማያደርግልንን ነገር በነዚህ ርእሶቻችን ዙሪያ ምላሽ አድርጎ ሊሰጠን የታመነ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ ጸሎት የሰጠውን የተስፋ ቃል በመታመን ይጸልዩ፡፡ የህ ከኛ የማይወሰድ ምርጫ ነው፡፡ “ማርታ ማርታ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ ትታወኪማለሽ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው ፤ ማርያምም አንድ እድልን መርጣለች ከእርሱአም አይወሰድባትም” (ሉቃ 10፡41-42) ማርያም በጌታ እግር ስር ሆና ቃሉን ስትማር ማርታ በጉአዳ በስራ ተጠምዳ ነበር፡፡ ኢየሱስም ማርያም ጥክክለኛውን ምርጫ መርጣለች ምክንይቱም የመረጠችው ምርጫ ከእርሱአ የማይወሰድ ስለሆነ ነው ብሉአል፡፡ የትኛውም ነገር ከኛ ሊወሰድ ይችላላ ከኢየሱስ ጋር የሚሆን ጊዜ ግን መቼም ቢሆን አይወሰድም ምክንያቱም አሁን ክርስቶስ ኢየሱስን የምንመግበው ልብ የሚጨምር ዘላለማዊ ደስታን ያመጣልሃል፡፡ በስራ ፣ በፌስ ቡክ ፣ በተለያዩ መጸሀፍት ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እየተፈተኑ ለእግዚአብሄር ጊዜን አጥተዋል፡፡ እነዚህን ሁሉ ያቁሙ፡፡ የማይወሰድ ሰላም ወደ ህይወቴ ሊያመጣ የሚችለው ምንድን ነው ብለው ራስዎን ይጠይቁ … ከዚያም በኢየሱስ እግር ስር ያለችውን ማሪያምን የቀላቀሉአትና ቃሉን ያድምጡ፡፡ ነገ ጠዋት የመቀስቀሻ ደውሉ ጠፍቱአል እየሞከርኩ ነው፡፡ ግን ትንሽ ልተኛ መሸለኝ፡፡ ቆይ … ቆይ ግን እግዚአብሄር እኮ ተዝቆ ወደማያልቅ ደስታ እየጋበዘኝ ነው ቃሉ እምነቴን ያጸናልኛል በዙሪያ ለከበበኝ ጨለማ ቃሉ ብርሀን ይሆንልኛል ስጸልይ ጌታ ጸሎቴን ይመልስልኛል ይህ እኮ የማይወሰድ ምርጫ ነው ስለዚህ ብነሳ ያዋጣኛል