አማን ስብሃት

የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው መዝሙር 116:15

ወንድማችን አማን ስብሃት የፓል ቶክ መጠሪያ ስሙ "YeNigat Kokeb"በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ማክሰኞ ሜይ 22 2007 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡እግዚእብሔር የወንድማችንን ቤተሰብ እንዲያጽናና እንጸልያለን


Psalim 116:15 Precious in the sight of the LORD is the death of his saints.
Our Dear brother Aman Sibhat "YeNigat Kokeb" who was a very dear brother to all of Us has passed away due to car accident on May 22 2007 in winnpeg Canada. we pray for the comfort of his parents and family.ሰላም ለናንተ ይሁን ቅዱሳን? እንደምን አላችሁ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን። በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ታላቅ ነውና። በእውነት ሁላችንም ብንሆን ስለ ንጋት ኮከብ ሞት አዝነን ነበር። ግን እግዚአብሔር በስራው አይሳሳትም። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ ትላንትናው ማለትም ሰኞ ቀን የቀብር ስነ ስርዓት በሆነበት ጊዜ ድረስ ቅዱሳን በያላችሁበት አዝናችሁ ስለነበር ይህንንም ነገር በቀጥታ ማስታላለፍ ስለወደድኩ በዚህ ሰዓት ደሞ አስተላልፋለሁ። ጌ እየሱስ ጌታ ነው! ወገኖቼ እኛ ማየት ያለብን ለምን ሆነ እንዴት ሆነ አይደለም። ለምን? የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው ፃድቅ ያልፋል የሚያስተውል ግን  ይላል። ስለዚህ እንድንናስተውል የእግዚአብሔር ሃሳብና ፍቃድ ነው። በዚህ ዘመን ወንድማችን ከመካከላችን በመጀመሪያ ቀን ሲለይ ሁላችንም አዝነን ነበር ግን በሁለተኛው ቀን ላይ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር በመካከላችን ሲያደርግ ስላየን ደስ ብሎናል። ይኽውም እንዴት ነው? በእኛና በኤርትራውያን መካከል ንግስት ባደረገው ሁኔታ ግኑኝነት አልነበረም እና ትልቅ የጥል ግድግዳ ነበር። ነገር ግን በንጋት ኮከብ ሞት ምክንያት እግዚአብሔርበቀን ሁለት ጊዜ ወንጌል በትግርኛና በአማርኛ ይሰበክ ነበር።

መገኛኘትም የማንችለውንም በአንድ አዳራሽ ውስጥ አስቀምጦ ይሄን የእግዚአብሔር መንግስት ሰራ እንዲስፋፋ አደረገ። በከተማችንም በድንቅ በታምራት ወንጌል ተሰበከ እኛም በጣም ደስ አለን። ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ነገሮችን በመልካም ቀየረው። ለምን ጻድቁን ወደ ራሱ ሰብስቦ ግን ለምንግስቱ ሰራ ምክንያቱም የሃጢያተኛውን ሞት የማይወደው እግዚአብሔር

ለሃጢያተኞች የንስሃ ጊዜ ሊሰጥ ስለወደደ ይህን አደረገ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን በዚህ ደሞ ልንጽናና ይገባናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ምን አለ እኔ ብሔድ ይሻለኛል ለምን በዛ የተሻለ ቦታ አለ አለ። ወደ ተሻለው ቦታ ደግሞ ሁላችንም ለመሄድ እንሻለን እንናፍቃለንና ሰው ወደተሻለ ቦታ ሲሄድ ደስ ይለዋል እኛም በዚህ ነገር ደስ ብሎናል። ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ከኛ ቢለይ ግን የእግዚአብሔር ስራ ሲሰራ አይተን ደስ ብሎናል።

እኛም ወደዚሁ ወደ ጌታ እንሰበሰባለን ምክንያቱም ወንድማችን ንጋት ኮከብ የድንኳኑን ዘመኑንና ጊዜውን ጨርሶ ወደ አምላኩ ተሰብስቧል እኛም በግዚአብሔር ጊዜ ለዘላለም እናየዋለን። በዚህ ምክንያት ለሰባት ቀን ነበር ሃዘኑ በቤተ ክርስቲያን የተደረገው ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ አዳራሽ ስላዘጋጀ ከዛ የተነሳ ለሰባት ቀን ቢያንስ ሁለቴና ሶስቴ ከዚያም በላይ ወንጌል እየተሰበከ በተለያየ ቋንቋ ሲፀለይና ሲሰበክ ሙሉ ቀን እስከ እኩለ ሌሊት አብረን ከወገኖች ጋር በከተማው አብረን አሳልፈናል ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። ወገኞቼ በጣም ደስ ይል ነበር በሃዘንም ለካ እንዲ ያለ ሁሌታ አለ? እግዚአብሔር ለእኛ የጥሞና ጊዜ ነው ያደረገልን። መሰራት የማይገባው ነገር ሁሉ ተሰርቷል:: እግዚአብሔር ትልቅ ነው። በዚህም ደስ ይለናል ምን ጊዜም በምድር ላይ መኖራችን ለወንጌል ነው። የንጋት ኮከብ በጣም ዝምተኛ እና ምንም የማይናገር በመካከላችን ቢሆንም ነገር ግን በአገልግሎቱ እንባረክ ነበር።

ሌላው ትላንትና (ሰኞ) የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል ከቀብሩ መጀመሪያ በቤተ ክርስቲያናችን አስክሬኑ መጥቶ ስነስራቱ ሲፈጸም ብዙ ዝብ በተሰበሰበት አፕስቲር እና ዳውንእስቴር ያለው አዳራሽ ሞልቶ ነበር። ወንጌል በተጨማሪም እኔም እናንተን በመወከል ‘ኢትዮጲያን ፕላስ ኦል’ የፍቅር መግለጫ አበርክቻለሁ። የኤ እና የ ቢ መዘምራን ቆመው ዘመሩ ለተወሰነ ጊዜ እንደሚላያይ ሰው ሸኝተው እንደሚመለስ በዚህ መልኩ ሽኝተነው ተመልሰን በጣም ደስ በሚል ሁሌታ ስነስርዓቱ ተካሂዷል:: አብረንም የፍቅር ማዕድ ቆረስንና በመጨረሻም እስከ እኩለ ሌሊት ቆይተን ተለያየን። በጣም የሚገርመው ሰው ከሃዘን ሲለያይ እያለቀሰ ነው እንጂ እንደሰርግ ቤት ፎቶ እየተነሳ አይለያይም እኛ ግን ከቤተሰቡ ጋር ማስታወሻ ይሆነን ዘንድ ይህንን አድርገን ተለያየን። ማንም ወንድሙ ወይም ቤተሰቡ ሞቶበት እንደዛ አያደርግም እግዚአብሔር ግን ይህንን አደረገ ስለዚህ እናንተም ልታዝኑና ልታለቅሱ አይገባም። ለምን እግዚአብሔር ፍጹም እና ፃድቅ ስለሆነ ለክብሩ ለመንግስቱ ስፋት አድርጓልም ወንጌልም በኃይል ተሰብኳል። ስለዚህ ተስፋ እንደሌላቸው አይደለም አንድ ቀን እንገኛልን። በእህቱ እና በቤተሰቦቹ ስም ምስጋና አቀርባለሁ።

የእህቱም ስም ‘ሃሌ ሉያ’ በሚል ኒክ መጠሪያ ስም የምትገባ ናት። እግዚአብሔር ይባርካችሁ ስለ ፍቅር ስጦታችሁ ብላለች።

የማስተላልፈው የአብ ሥራ ነኝ ከካናዳ