ወንድም ተወልደ ዮሐንስ

ወንድም ተወልደ ዮሐንስ ከአባታቸው ከአቶ ዮሐንስ ተመልሶና ከእናታቸው ከወይዘሮ .ድስታ መድህኔ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የካቲት 24 ቀን 1938 ዓ.ም ሰገነይቲ በተባለው ከተማ ተወለዱ፡፡ዕድሜያቸው ለትምሕርት አንደደረሰ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኤርትራና በትግራይ ከተከታተሉ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በትግራይ አጠናቀው በ1956 ዓም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ1961 ዓ.ም ከፊዚክስ ዲፓርትመንት በባችለር ኦቭ ሳይንስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡በወቅቱ በነበረው ስርዓት መመሪያ ዬኒቨርሲቴ ተማሪዎች ተምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት የአንድ ኣመት የአገልግሎት ጊዜ መስጠት ስለነበረባቸው በ1960 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተመድበው አገልግለዋል፡፡

 

ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደስራ ዓለም በመሰማራት ከነሐሴ 1961 እስከ መስከረም 1971 ድረስ በአስበ ተፈሪ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነት

ከመስከረም 1963 እስከ እስከ ህዳር 1969 ድረስ በድሬዳዋ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነትና በምክትል ዲሬክተርነት

ከህዳር 1969 እስከ እስከ መስከረም 1 1978 በአዲስ አበባ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስተማሪነትና በምክትል ዲሬክተርነት

ከኦገስት 1998 እስከ ጁላይ 2007 በበኹም ጀርመን በድህረ ምረቃ ትምህርትና በምርምር .ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በጀርመን አገር ቆይታቸውም በፊዚክስ የ.ማስተርስ ዲግሪያቸውን የሰሩ ሲሆን ዶክተሬት ዲግሪቸወወን ሰርተው በማተናቀቅ ላይ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም በኮምፒዩተር ሳይንስና በበርካታ የድኅረ ምረቃ ኮርሶች የምስክር ወረቀቶችን ተቀብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ነጻነት ባልነበረበት የደርግ ስርዓት እንዴት በክርስትና ህይወት እንዳሰለፉ ባለቤታቸው እህት ገነት እሸቴ እንዲህ በማለት ይገልጹታል.... ተወልደ ዮሐንስ በአዲስ አበባ የሕይወት ብርሃን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሆኖ ሰርቷል፡፡ በዚያን ጊዜ በደርግ ስርዓት መሠረተ ትምህርት በየቀኑ ማታና እሁድ ጠዋት ማስተማር ግዴታ ነበር፡፡ ወንድም ተወልደ ግን

የእሁድ ጠዋቱ የማስተማር ፕሮግራም ከቤተ ክርስቲያን ስለሚያስቀረው አያስተምርም ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ከደርግ ጋር ብዙ ችግር ፈጥሮበት ነበር፤ በከፍተኛ፣ በቀበሌና በመጨረሻ ላይ 3ኛ በተባለው ሰውን እየወሰዱ በሚጨርሱበት ቦታ ሁሉ ታስሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ መርማሪው ፖሊስ ለምን እሁድ ጠዋት መሠረተ ትምህርት እንደማያስተምር ሲጠይቀው በቤተክርስቲያን

የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምራቸው ሰዎች ስላሉ እንደሆነ መለሰለት፡፡ በዚያን ጊዜ ፖሊሱ አንተ እዚያ የምታስተምረውን ነገር እኔም ድሮ እማር ነበር፤ አንተ ሃቀኛ ሰው ነህ ብሎ ከ3 ቀን በኋላ ከእስር ፈታው፡፡

በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ፖሊሶችና ካድሬዎች የትምህርት ቤቱን ቻፕል ለደርግ የስብሰባ አዳራሽ መጠቀሚያ ለማድረግ ካልሰጠኸን ብለው ሲመጡ፤ እንዲሁም ክርስቲያኖችን በእምነታቸው ምክንያት ለመያዝ ሲመጡ በእኔ ደም ተራምዳችሁ ነው ይህን የምታደርጉት ብሎ ሁልጊዜ በድፍረት ጠመንጃ ከያዙ ሰዎች ጋር ከፊት የሚጋፈጥ ሰው ነበር፡፡ በጌታ እጅግ ስለሚተማመንና በዚህ ድፍረቱ

አዳራሹን ደርግ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

በድሬዳዋ ልዑል መኮንን ትምህርት ቤት ምክትል ዳይሬክተርና መምህር ሳለ፣ ተማሪዎችን ትምሕርት ሲያቆሙ መማርና መሥራት እንዳለባቸው ሲያደፋፍር ተማሪዎች ከፎቅ ላይ እባብ ወርውረውበት ነገር ግን ምንም ሳይሆን ተርፏል፡፡

2ኛዋ ልጃችን በሁለት አመቷ አባቷን በጠመንጃ አስፈራርተው በጂፕ መኪና ሲወስዱት ስላየች እስካሁን ድረስ የወታደር ልብስ እንኳ ስታይ ትረበሻለች በማለት ገልጸውልኛል፡፡

ወንድም ተወልደ ዮሐንስ በቅርብ ለሚያውቃቸውና ለተጠጋቸው ብቻ ሳይሆን በአጪር ጊዜ ቅርበት ብቻ ለተጠጋቸው ሰው በእርግጥም ራሳቸው የሚነበቡ ወንጌል መሆናቸውን ለመረዳት ብዙም አይወስድበትም፡፡

ወንድም ተወልደ በመላው አውሮፓ በተቋቋሙት የክርስቶስ ቤተክርስቲያናት ውስጥ በችግርም ሆነ በደስታ ጊዜ ቀድመው በመገኘት በአርአያነት የሚጠቀሱ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው የአምነት አባትና ሃዋርያ ነበሩ፡፡ ወንድም ተወልደ ዮሐንስ ከባለቤታቸው ከእህት ገነት እሸቴ ሕድዓት : ምስጋና,አወት,ምህረትና,ዘካርያስ የሚባሉ 5 ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ምንም እንኳን ወንድም ተወልደ ዮሃንስ በአባታቸው ዕቅፍ ውስጥ ለዘለዓለም ለመኖር በድል የተሰናበቱን ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው መሆናቸውን በማሰብ ብንጽናናም በአውሮፓ የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያንና መላው ዓለም የሚገኙ ወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በክርስቶስ የሆኑ ወገኖቻቸው ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፤ታላቅ ወንደም መካሪና አጽናኝና አጥተዋል፡

፤እግዚአብሔር መጽናናትን ለቅዱሳን ሁሉ እንዲሰት ጸሎታችን ነው፡